ዘፍጥረት 3:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው አራዊት ሁሉ፥ እባብ እጅግ ተንኰለኛ ነበረ፤ ስለዚህ እባብ “በአትክልቱ ቦታ ካሉት ዛፎች ሁሉ ፍሬ እንዳትበሉ በእርግጥ እግዚአብሔር አዞአችኋልን?” ሲል ሴቲቱን ጠየቃት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እባብ እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው የዱር አራዊት ሁሉ ተንኰለኛ ነበረ፤ ሴቲቱንም፣ “በርግጥ እግዚአብሔር፣ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ዛፎች ከማናቸውም እንዳትበሉ’ ብሏልን?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ አንዳች እንዳትበሉ አዝዞአልን?” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው ከምድር አራዊት ሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነበር። እባብም ሴቲቱን “እግዚአብሔር በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ አትብሉ ያላችሁ ለምንድን ነው?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኵለኚ ነበረ። ሴቲቱንም፤ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአል? አላት። |
በዚያን ቀን እግዚአብሔር በጽኑ፥ በታላቁና በኀያል ሰይፉ የሚስለከለከውንና የሚጠመጠመውን እባብ ሌዋታንን ይቀጣል፤ የባሕሩንም ዘንዶ ይገድላል።
“ ‘እግሮችህ በድንጋይ እንዳይሰናከሉ፥ በእጆቻቸው ይደግፉህ ዘንድ መላእክቱን ያዝልሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ፥ ከዚህ ወደታች ራስህን ወርውር” አለው።
እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት ምናልባት የእናንተም ሐሳብ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ያላችሁን ቅንና ንጹሕ የሆነ ታማኝነት ትተዋላችሁ ብዬ እፈራለሁ።
እናንተም ባሎች! ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ከእናንተ ይልቅ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑና ከእናንተም ጋር የሕይወትን ጸጋ ስለሚወርሱ አክብሩአቸው፤ በዚህ ዐይነት ለጸሎታችሁ መሰናክል የሚሆን ነገር አይኖርም።
ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።