ዘፍጥረት 26:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የይስሐቅ አባት አብርሃም በሕይወት በነበረበት ዘመን የእርሱ አገልጋዮች ቆፍረዋቸው የነበሩትን የውሃ ጒድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ የተነሣ ፍልስጥኤማውያን፣ አባቱ አብርሃም በሕይወት በነበረበት ጊዜ፣ የአብርሃም አገልጋዮች የቈፈሯቸውን የውሃ ጕድጓዶች በሙሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኗቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአባቱ በአብርሃም ዘመን የአባቱ ሎሌዎች የማሱአቸውን ጉድጓዶች ሁሉ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑአቸው፥ አፈርንም ሞሉባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአባቱ በአብርሃም ዘመን የአባቱ ሎሌዎች የማሱአቸውን ጕድጓዶች ሁሉ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑአቸው፤ አፈርንም ሞሉባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአባቱ በአብርሃም ዘመን የአባቱ ሎሌዎች የማሱአቸውን ጕድጓዶች ሁሉ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑአቸው አፈርንም ሞሉባቸው። |