ዘፍጥረት 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ፥ ከምድር ውስጥ ምንጭ ፈልቆ የብሱን ሁሉ ያጠጣ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ውሃ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የውኃ ምንጭ ከምድር ይወጣ ነበር፤ የምድርንም ፊት ሁሉ ያጠጣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤ ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፤ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።