ዘፍጥረት 2:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ወንዝ ፊሶን ይባላል፤ እርሱም ወርቅ በሚገኝበት ሐዊላ በሚባለው ምድር ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመጀመሪያው፣ ወርቅ በሚገኝበት በኤውላጥ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የፊሶን ወንዝ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፥ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የሐዊላን ምድር ይከብባል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአንደኛው ወንዝ ስም ኤፌሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአንደኚው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው። |
የእስማኤል ዘሮች ከግብጽ በስተምሥራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር፤ የኖሩትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዘሮች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ በሐሰትና በማታለል ከበውኛል፤ ይሁዳ ግን አሁንም እኔ በእግዚአብሔር በምመራው መንገድ ይሄዳል፤ ለእኔ ለቅዱሱም ታማኝ ነው።