ዘፍጥረት 18:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ አሁንም እንደገና በመናገሬ ይቅር በለኝ፤ ምናልባት ኻያ ቢገኙስ?” አለ፤ እግዚአብሔርም “ኻያ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃምም፣ “ከጌታዬ ጋራ እናገር ዘንድ መቼም አንዴ ደፍሬአለሁና ምናልባት ሃያ ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እርሱም፣ “ሃያ ቢገኙ፣ ለእነርሱ ስል እምራታለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም፦ “እነሆ፥ ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፥ ምናልባት ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም፥ “እነሆ፥ ከጌታዬ ከእግዚአብሔር ጋር እነጋገር ዘንድ ባለሟልነትን ካገኘሁ ከዚያ ሃያ ቢገኙሳ?” አለው። እርሱም፥ “ስለ ሃያው አላጠፋትም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም፤ እነሆ ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤ ምናልባት ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ? አለ። እርሱም፤ ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም አለ። |
አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ እባክህ አትቈጣ፤ እንደገና ልናገር፤ ምናልባት ሠላሳ ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እግዚአብሔርም “ሠላሳ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።
አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ እባክህ አትቈጣ አንድ ጊዜ ልናገር፤ ዐሥር ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እግዚአብሔርም “ዐሥር ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።
እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፥ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ፤ ታዲያ፥ በሰማይ ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን አይሰጣቸውም!
እንግዲህ ምሕረት እንድንቀበልና ርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋ እንድናገኝ ጸጋው ወደሚገኝበት ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ያለ አንዳች ፍርሀት እንቅረብ።