Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 18:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ደግሞም፦ “እነሆ፥ ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፥ ምናልባት ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 አብርሃምም፣ “ከጌታዬ ጋራ እናገር ዘንድ መቼም አንዴ ደፍሬአለሁና ምናልባት ሃያ ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እርሱም፣ “ሃያ ቢገኙ፣ ለእነርሱ ስል እምራታለሁ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ አሁንም እንደገና በመናገሬ ይቅር በለኝ፤ ምናልባት ኻያ ቢገኙስ?” አለ፤ እግዚአብሔርም “ኻያ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ደግ​ሞም፥ “እነሆ፥ ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እነ​ጋ​ገር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ካገ​ኘሁ ከዚያ ሃያ ቢገ​ኙሳ?” አለው። እር​ሱም፥ “ስለ ሃያው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ደግሞም፤ እነሆ ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤ ምናልባት ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ? አለ። እርሱም፤ ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም አለ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 18:31
10 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ ምሕረት እንድንቀበልና ርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋ እንድናገኝ፥ ጸጋው ወደሚገኝበት በመታመን እንቅረብ።


በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ እስከ መጨረሻው በጽናት ትጉ።


ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንደሚገባቸው የሚያስተምር ምሳሌን ነገራቸው፤


እላችኋለሁ፤ ወዳጁ ስለ ሆነ እንኳ ተነሥቶ ባይሰጠው፥ ስለ ንዝነዛው ግን ተነሥቶ የሚፈልገውን ያህል ይሰጠዋል።


እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካም ነገርን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም!


“ጠይቁ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል።


አብርሃምም መለሰ ዓለም፦ “እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፥


እርሱም፦ “ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ከዚያ ሰላሳ ባገኝ አላጠፋም” አለ።


እርሱም፦ “እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፥ ምናልባት ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ስለ አሥሩ አላጠፋትም” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios