ዘፍጥረት 18:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከተማይቱ ውስጥ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን በሙሉ ትደመስሳለህን? ስለ ኀምሳው ደጋግ ሰዎች ስትል ከተማይቱ እንዳትጠፋ አታደርግምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ቢገኙ፣ በውኑ ነዋሪዎቹን ሁሉ ታጠፋለህን? በውስጧ ለሚገኙ ዐምሳ ጻድቃን ስትል ከተማዪቱን ይቅር አትልምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህን? ከተማይቱንስ በእርሷ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማዪቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህብ? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? |
በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ እባክህ አትቈጣ አንድ ጊዜ ልናገር፤ ዐሥር ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እግዚአብሔርም “ዐሥር ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! “እስቲ በኢየሩሳሌም መንገዶች ሁሉ እየተዘዋወራችሁ እዩ! ትክክለኛ ፍርድ የሚሰጥና እውነትን የሚሻ አንድ ሰው እንኳ ማግኘት ትችሉ እንደ ሆነ፥ እስቲ በየአደባባዩ ፈልጉ! ይህ ቢሆን እኔ ለኢየሩሳሌም ምሕረት አደርግላታለሁ።
‘ጳውሎስ ሆይ! አትፍራ! በሮም ንጉሠ ነገሥት ፊት መቆም ይገባሃል! እነሆ፥ ከአንተ ጋር የሚጓዙትንም ሁሉ እግዚአብሔር ለአንተ ብሎ ከሞት ያድናቸዋል’ ብሎ ነግሮኛል።