አብራም የወንድሙ ልጅ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ ተወልደው የጦር ልምምድ ያላቸውን 318 ሰዎች በትጥቅ አደራጅቶ አራቱን ነገሥታት በመከታተል እስከ ዳን ድረስ ሄደ።
ዘፍጥረት 17:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃል ኪዳኔ ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር የሚኖር መሆኑን የሚያሳይ የሥጋ ምልክት እንዲሆን እያንዳንዱ ወንድ ይገረዝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቤትህ የተወለደም ሆነ በገንዘብህ የተገዛ ሁሉ መገረዝ አለበት፤ በሥጋችሁ የሚፈጸመው ይህ ኪዳኔ የዘላለም ኪዳን ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤትህም የተወለደ፥ በብርም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። |
አብራም የወንድሙ ልጅ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ ተወልደው የጦር ልምምድ ያላቸውን 318 ሰዎች በትጥቅ አደራጅቶ አራቱን ነገሥታት በመከታተል እስከ ዳን ድረስ ሄደ።
“በአንተና በዘርህ፥ በመጪውም ትውልድ መካከል ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም አጸናለሁ፤ በዚህም ዐይነት ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
እርሱ የሥጋ ወንድማችን ስለ ሆነ” በእርሱ ላይ ጒዳት ከምናደርስበት ይልቅ ለእነዚህ እስማኤላውያን ነጋዴዎች ብንሸጠው ይሻላል፤ ወንድሞቹም በዚህ ሐሳብ ተስማሙ።
በዚያን ጊዜ የምድያም ሰዎች እስማኤላውያን ዮሴፍን በግብጽ አገር ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር ከፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነ የዘበኞቹ አለቃ ነበር።
እስማኤላውያን ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት፤ እዚያም ከግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ ለሆነው ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር የተባለው ግብጻዊ፥ የፈርዖን የዘበኞች አለቃ ነበር።
ቀስት በደመናዎች ላይ በሚታይበት ጊዜ ተመልክቼ በእኔና በምድር ላይ ባሉት ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያለውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።”
ከአይሁድ ወገኖቻችን ጋር ዘራችን አንድ ነው፤ የእኛ ልጆች ከእነርሱ ልጆች የሚለዩበት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ የገዛ ልጆቻችንን ለባርነት አሳልፈን ለመስጠት ተገደናል፤ እንዲያውም ከሴቶች ልጆቻችን አንዳንዶቹ ባሪያዎች ሆነዋል፤ ነገር ግን እርሻችንና የወይን ተክል ቦታችን ስለ ተወሰዱ ኀይል የሌለን ሆነናል” በማለት አቤቱታ አሰሙ።
“ለአሕዛብ ሕዝቦች የተሸጡ አይሁድ ወገኖቻችንን ራሳችን ልንቤዣቸው በማሰብ የሚቻለንን ሁሉ አደረግን፤ እናንተ ደግሞ እነሆ፥ የገዛ ወንድሞቻችሁ የሆኑት አይሁድን ወገኖቻቸው ለሆናችሁት ለእናንተ ባርያዎች አድርገው ራሳቸውን እንዲሸጡላችሁ በማድረግ ላይ ትገኛላችሁ!” ብዬ ገሠጽኳቸው፤ መሪዎቹም የሚመልሱት ቃል አጥተው ዝም አሉ።
ጌታው ሚስት የምትሆነው ሴት ሰጥቶት ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወልዳለት ከሆነ ሴትዮዋ ከነልጆችዋ የጌታው ትሁን፤ ሰውየው ግን ብቻውን ነጻ ይውጣ።