ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
ዘፍጥረት 13:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሎጥ መላውን የዮርዳኖስን ሸለቆ ለራሱ መረጠና ወደ ምሥራቅ ሄደ፤ ሁለቱ የተለያዩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ በሙሉ መርጦ ወደ ምሥራቅ አመራ፤ ሁለቱ ሰዎች በዚሁ ተለያዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ፥ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፥ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተለያዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎጥም ለራሱ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን ሀገር ሁሉ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተለያዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ ሎጥም ወደ ምሥርቅ ተጓዘ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተሰያዩ። |
ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ተለይተህ ሂድ፤ አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።”
ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው።
ወዳጆችህን ወይም የአባትህን ወዳጆች አትርሳ፤ ችግር ሲደርስብህ የወንድምህን ርዳታ አትጠይቅ፤ ከሩቅ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጐረቤት ይጠቅምሃል።
“የምሥራቁ ድንበር በደማስቆና በሐውራን መካከል አልፎ በዮርዳኖስ በኩል፥ በጊልዓድና በእስራኤል ምድር መካከል አልፎ ወደ ሙት ባሕርና እስከ ታማር ድረስ ነው። ይህም የምሥራቁ ድንበር ይሆናል።
ዘወትር እየተገናኘን እርስ በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ።