ዘፍጥረት 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጎሜር ልጆች፦ አሽከናዝ፥ ሪፋትና ቶጋርማ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጎሜር ልጆች፦ አስከናዝ፣ ሪፋት፣ ቶጋርማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጎሜር ልጆች፦ አሽከናዝ፥ ሪፋት እና ቶጋርማ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው። |
“አደጋ ለመጣል የሚያስችል ምልክት ስጡ! ሕዝቦች ሁሉ መስማት እንዲችሉ እምቢልታ ንፉ! ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ! የአራራት፥ የሚኒና የአሽኬናዝ መንግሥታት አደጋ እንዲጥሉ ንገሩአቸው፤ የጦር አዛዥ የሚሆን ሰው ሹሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ፈረሶችን አምጡ።
ጎሜር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋርና፥ ራቅ ካለው የሰሜን ክፍልም ቤት ቶጋርማና ሠራዊቱ ከእርሱ ጋር ናቸው፤ እንዲሁም ከሌሎች ብዙዎች አገሮች የመጡ ሰዎች ከእርሱ ጐን ተሰልፈዋል።