ገላትያ 4:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያ ጊዜ የምሥራቹን ቃል ለእናንተ ለመስበክ ዕድል ያገኘሁት በሕመም ላይ በነበርኩበት ጊዜ መሆኑን ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደምታውቁት፣ በመጀመሪያ ለእናንተ ወንጌልን የሰበክሁት በሕመም ምክንያት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀድሞ በሥጋ ድካም ወንጌልን እንደሰበክሁላችሁ ታውቃላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጀመሪያ ወንጌልን በሰበክሁላችሁ ጊዜ፥ ከሥጋ ድካም የተነሣ እንደ ነበር ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያ ወንጌልን በሰበክሁላችሁ ጊዜ ከሥጋ ድካም የተነሣ እንደ ነበረ ታውቃላችሁ፥ |
ኢየሱስም በምኲራቦቻቸው እያስተማረና የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፥ በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የተያዙትንም ሰዎች እየፈወሰ በገሊላ ምድር ሁሉ ይዘዋወር ነበር።
ምናልባት አንዳንዶች “የጳውሎስ መልእክቶች ከባዶችና ብርቱዎች ናቸው፤ እርሱ ራሱ ከእኛ ጋር ሲሆን ግን ደካማ ነው፤ ንግግሩም የተናቀ ነው” ይሉ ይሆናል።
እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተው በደካማነት ቢሆንም አሁን በእግዚአብሔር ኀይል በሕይወት ይኖራል፤ እኛም ከእርሱ ጋር ደካሞች ሆነናል፤ ከእናንተ ጋር ባለን ግንኙነት ግን ከእርሱ ጋር በእግዚአብሔር ኀይል እንኖራለን።
ምንም እንኳ ሕመሜ ፈተና ቢሆንባችሁ አልናቃችሁኝም ወይም አልተጸየፋችሁኝም፤ እንዲያውም የእግዚአብሔርን መልአክ እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ ተቀበላችሁኝ፤ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ ተቀበላችሁኝ።