La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 8:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሁሉም ነገር በዚያኑ ሰዓት ተቈጥሮና ተመዝኖ በትክክል ተመዘገበ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሁሉም ነገር ተቈጠረ፤ ተመዘነም፤ የተመዘነውም ሁሉ በዚያ ጊዜ ተመዘገበ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያን ሰዓት ሁሉም ነገር ተመዘነ፤ በሚዛንና በቍጥር ም ተመዘገበ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁሉም በቍ​ጥ​ርና በሚ​ዛን ተመ​ዘነ፤ ሚዛ​ኑም ሁሉ በዚያ ጊዜ ተጻፈ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁሉም በቍጥርና በሚዛን ተመዘነ፤ ሚዛኑም ሁሉ በዚያን ጊዜ ተጻፈ።

Ver Capítulo



ዕዝራ 8:34
3 Referencias Cruzadas  

ወደ ቤተ መቅደስ መግባት እስኪችሉ ድረስ በጥንቃቄ ጠብቁአቸው፤ እዚያም ለካህናቱ በተመደበው ክፍል ውስጥ እነዚህን ሁሉ ንዋያተ ቅድሳት መዝናችሁ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ መሪዎች እንዲሁም በኢየሩሳሌም ለሚገኙት የሕዝቡ መሪዎች አስረክቡአቸው።”


ከዚህም በኋላ በአራተኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ሄድን፤ ብሩን፥ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱንም ሁሉ መዝነን ለኡሪያ ልጅ ለካህኑ ለመሬሞት አስረከብነው፤ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛርና እንዲሁም ሌዋውያኑ ዮዛባድ ተብሎ የሚጠራው የኢያሱ ልጅና ኖዓዲያ ተብሎ የሚጠራው የቢኑይ ልጅ ከእርሱ ጋር አብረው ነበሩ።


ከዚያም ቀጥሎ እነዚያ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን መባ ሁሉ አመጡ፤ በዚህ ዐይነት በመላው እስራኤል ሕዝብ ስም ዐሥራ ሁለት ኰርማዎችን፥ ዘጠና ስድስት የበግ አውራዎችንና ሰባ ሰባት የበግ ጠቦቶችን አቀረቡ፤ እንዲሁም ስለ ኃጢአታቸው ስርየት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ፤ እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ።