ዕዝራ 5:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የተባበሩአቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ለማወቅም ጠየቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም፣ “ይህን ሕንጻ የሚገነቡት ሰዎች ስም ማን ይባላል?” በማለት ጠየቋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም፦ “ይህንስ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ስም ማን ነው?” ብለው ጠየቁአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም፥ “ይህችን ከተማስ የሚሠሩ ሰዎች ስም ማን ማን ነው?” ብለው ጠየቁአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም፦ “ይህንስ ሥራ የሚሠሩት ሰዎች ስም ማን ነው?” ብለው ጠየቁአቸው። |
“ባጽልኤልና ኦሆሊአብ እንዲሁም ለተቀደሰው ድንኳን ዝግጅት እግዚአብሔር ማናቸውንም ሥራ ለመሥራት ችሎታንና ዕውቀትን የሰጣቸው ሌሎች ሰዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ይሠራሉ።”