የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ እነዚያን ንዋያተ ቅድሳት ሚትረዳት ተብሎ በሚጠራው በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ አስቈጥሮ የይሁዳ ገዢ ለሆነው ለሼሽባጻር አስረከበው፤
ዕዝራ 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮጼዴቅ ልጅ ኢያሱም የነዚህን ነቢያት የትንቢት ቃል በሰሙ ጊዜ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ቤተ መቅደስ መሥራታቸውን እንደገና ቀጠሉ፤ ሁለቱ ነቢያትም ይረዱአቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራት ተነሡ፤ የሚያግዟቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ዐብረዋቸው ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸው የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል እና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ። |
የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ እነዚያን ንዋያተ ቅድሳት ሚትረዳት ተብሎ በሚጠራው በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ አስቈጥሮ የይሁዳ ገዢ ለሆነው ለሼሽባጻር አስረከበው፤
ከባዕዳን ሴቶች ጋር የተጋቡ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮጼዴቅ ልጆች ከሆኑት ከኢያሱና ከወንድሞቹ ጐሣ የተገኙ፤ ማዕሤያ፥ ኤሊዔዘር፥ ያሪብና ገዳልያ፤
የኢዮጼዴቅ ልጅ ኢያሱም ከወገኖቹ ካህናትና የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልም ከዘመዶቹ ጋር በመተባበር የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንደገና ሠሩ፤ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ በተጻፈውም መመሪያ መሠረት በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ ቻሉ።
ስለዚህም በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ወደነበረበት ስፍራ በደረሱበት በሁለተኛው ዓመት፥ በሁለተኛው ወር፥ ዘሩባቤል፥ ኢያሱና ሌሎቹም የሀገራቸው ልጆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ባጠቃላይም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የመጡት ምርኮኞች ሥራውን ጀመሩ። ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ሌዋውያን ሁሉ የቤተ መቅደሱ ሕንጻ ሥራ ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ።
የአይሁድ መሪዎች፥ ነቢያቱ ሐጌና ዘካርያስ እያበረታቱአቸው የቤተ መቅደሱን ሥራ አፋጠኑት፤ በእስራኤል አምላክ ፈቃድ የፋርስ ነገሥታት ቂሮስ፥ ዳርዮስና አርጤክስስ ባዘዙትም መሠረት የቤተ መቅደሱን ሥራ ፈጸሙ፤
እነሆ ዘጠነኛው ወር ከገባ ከዛሬ ከኻያ አራተኛው ቀን ጀምሮ አስተውሉ፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት ከተጣለበት ቀን ጀምሮ አስተውሉ።
“ለሠራዊት አምላክ ቤተ መቅደስን እንደገና ለመሥራት መሠረት በተጣለበት በቅርብ ጊዜ የነበሩ ነቢያት የተናገሩትን ቃል የሰማችሁ እናንተ አይዞአችሁ በርቱ!