“እነርሱም እንዲህ ሲሉ አስረድተውናል፤ ‘እኛ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የታላቁ እግዚአብሔር አገልጋዮች ነን፤ ስለዚህም ለእርሱ ከብዙ ዘመን በፊት በአንድ ታላቅ የእስራኤል ንጉሥ ተሠርቶለት የነበረውን ቤተ መቅደስና ቅጽር እንደገና መልሰን በመሥራት ላይ እንገኛለን፤
ዕዝራ 5:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚህ ሥራ መሪዎችም እነማን እንደ ሆኑ እንገልጥልህ ዘንድ የስም ዝርዝራቸውን ጠይቀናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመሪዎቻቸውን ስም በጽሑፍ እናሳውቅህ ዘንድ ስማቸውን ደግሞ ጠየቅን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም እንድታውቅ፥ በእነርሱ ላይ ያሉትን መሪዎች ስም እንድንጽፍልህ ስማቸውን ጠየቅን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም እናስታውቅህ ዘንድ፥ በእነርሱም ያሉትን ሹሞች ስም እንጽፍልህ ዘንድ ስማቸውን ጠየቅን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም እናስታውቅህ ዘንድ፥ በእነርሱም ያሉትን ሹሞች ስም እንጽፍልህ ዘንድ ስማቸውን ጠየቅን። |
“እነርሱም እንዲህ ሲሉ አስረድተውናል፤ ‘እኛ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የታላቁ እግዚአብሔር አገልጋዮች ነን፤ ስለዚህም ለእርሱ ከብዙ ዘመን በፊት በአንድ ታላቅ የእስራኤል ንጉሥ ተሠርቶለት የነበረውን ቤተ መቅደስና ቅጽር እንደገና መልሰን በመሥራት ላይ እንገኛለን፤