ዘፀአት 8:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን “የምድሩን ትቢያ በበትሩ እንዲመታ ለአሮን ንገረው፤ በግብጽም አገር ሁሉ ትቢያው ወደ ተናካሽ ትንኝነት ይለወጣል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “አሮንን ‘በትርህን ሰንዝረህ የምድርን ትቢያ ምታ’ በለው፤ ከዚያም በግብጽ ምድር ያለው ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ይሆናል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን አለው፦ “ማልደህ ተነሣ፥ በፈርዖንም ፊት ቅረብ፤ እነሆ እርሱ ወደ ውኃ ይወርዳል፤ እንዲህም በለው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አሮንን፦ ‘በትርህን በእጅህ ዘርጋ፤ የምድሩንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማልም በግብፅ ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ይወጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ “አሮንን፦ ‘በትርህን ዘርጋ፤ በግብፅም አገር ሁሉ ቅማል እንዲሆን የምድሩን ትቢያ ምታ፤’ በለው።” |
እኔም ይህ ልጄ እኔን ያመልክ ዘንድ እንድትለቀው ነገርኩህ፤ አንተ ግን እምቢ አልክ፤ ስለዚህ አሁን የአንተን የበኲር ልጅ እገድላለሁ።’ ”
ከዚያም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ግብጽ ንጉሥ ሄደው “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘በበረሓ ለእኔ በዓል ለማድረግ እንዲሄዱ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይልሃል” አሉት።
እንደተባሉትም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘርግቶ በበትሩ የምድሩን ትቢያ መታ፤ በግብጽ አገር ያለውም ትቢያ ሁሉ ወደ ተናካሽ ትንኝነት ተለወጠ፤ ሰዎችንና እንስሶችንም ሁሉ ሸፈነ።
አስማተኞቹ በአስማታቸው ተጠቅመው ተናካሽ ትንኝ እንዲፈላ ለማድረግ ሞከሩ፤ ነገር ግን አልተሳካላቸውም፤ ተናካሽ ትንኝም በሰዎችና በእንስሶች ላይ ተሠራጨ።
እግዚአብሔርም ሙሴን “ጓጒንቸሮች ወጥተው መላውን የግብጽ ምድር ይሸፍኑ ዘንድ በወንዞች፥ በመስኖ ቦዮችና በኲሬዎች ሁሉ ላይ በትሩን እንዲዘረጋ ለአሮን ንገረው” አለው።