ዘፀአት 40:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በዚያ በእግዚአብሔር ፊት መብራቶቹን አበራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዳዘዘውም መብራቶቹን በእግዚአብሔር ፊት አበራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ቀንዲሎቹን በጌታ ፊት አበራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀንዲሎቹንም በእግዚአብሔር ፊት አበራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀንዲሎቹን በእግዚአብሔር ፊት ለኰሰ። |
ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጡ ነበር፤ በዙፋኑ ፊት የሚበሩ ሰባት ችቦዎች ነበሩ፤ እነርሱ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።