ዘፀአት 40:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የተቀደሰ ኅብስት በገበታው ላይ አሰናዳ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ኅብስቱን በላዩ ላይ በእግዚአብሔር ፊት አኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ኅብስቱን በላዩ በጌታ ፊት አሰናዳ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኅብስተ ገጹንም በላዩ በእግዚአብሔር ፊት አሰናዳ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጀራውን በላዩ በእግዚአብሔር ፊት አሰናዳ። |
ኅብስቱን በእግዚአብሔር ፊት ባለው በንጹሕ ወርቅ በተለበጠው ገበታ ላይ ስድስቱን በአንድ በኩል፥ ስድስቱን በሌላ በኩል በሁለት ረድፍ ደርድረህ አኑር።
እርሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር እርሱም ሆነ አብረውት የነበሩት ሰዎች ሊበሉት ያልተፈቀደውን፥ የተቀደሰ ኅብስት በላ።
ሁለት ክፍሎች ያሉአት ድንኳን ተዘጋጅታ ነበር። መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት የነበረባት መጀመሪያይቱ ክፍል “ቅድስት” ትባል ነበር።