Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 24:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ኅብስቱን በእግዚአብሔር ፊት ባለው በንጹሕ ወርቅ በተለበጠው ገበታ ላይ ስድስቱን በአንድ በኩል፥ ስድስቱን በሌላ በኩል በሁለት ረድፍ ደርድረህ አኑር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እነዚህንም ስድስት ስድስቱን በሁለት ረድፍ በእግዚአብሔር ፊት ባለው የንጹሕ ወርቅ ጠረጴዛ ላይ አኑራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እነዚህንም ስድስት ስድስቱን በሁለት ተርታ አድርገህ በጌታ ፊት በንጹሕ ወርቅ በተለበጠው ገበታ ላይ አኑራቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እነ​ዚ​ህ​ንም ስድ​ስት ስድ​ስ​ቱን በሁ​ለት ተርታ አድ​ር​ገህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በን​ጹሕ ገበታ ላይ አኑ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እነዚህንም ስድስት ስድስቱን በሁለት ተርታ አድርገህ በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ ገበታ ላይ አኑራቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 24:6
13 Referencias Cruzadas  

ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰሎሞን የሚከተሉትን ዕቃዎች አሠራ፤ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ፥


በየቀኑ ጧትና ማታ መዓዛው ጣፋጭ የሆነውን ዕጣንና የሚቃጠለውን የእንስሳት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያሳርጋሉ፤ በነጻው ገበታም ላይ የመባ ኅብስት ያቀርባሉ፤ ዘወትር ማታ ማታም ከወርቅ በተሠራው መቅረዝ ላይ ያሉትን ቀንዲሎች ያበራሉ፤ እኛ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንፈጽማለን፤ እናንተ ግን እግዚአብሔርን ትታችኋል።


እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ የሚከተሉትን ዕቃዎች ከወርቅ አሠርቶአል፦ መሠዊያውና ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ ጠረጴዛ፥


እንዲሁም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ከዚህ የሚከተሉትን ነገሮች አሟልተን እናቀርባለን፦ ይኸውም የተቀደሰውን ኅብስት፥ በየዕለቱ መቅረብ የሚገባውን የእህል መባ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆኑትን እንስሶች፥ በሰንበት ቀኖች፥ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ጊዜና በሌሎችም በዓላት የሚቀርበውን፥ ሌላውንም የተቀደሰ መባ ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ ኃጢአት ማስተስረያ መቅረብ የሚገባውንና ለቤተ መቅደሱ የሚያስፈልገውን ሌላውንም ነገር ሁሉ አናስታጒልም።


በሕጉ ስለ መሥዋዕት በተጻፈው መሠረት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መሥዋዕት የሚቃጠልበትን የማገዶ እንጨት የትኞቹ ጐሣዎች ማቅረብ እንደሚገባቸው እኛ ሕዝቡ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ በየዓመቱ ዕጣ በማውጣት እንወስናለን።


ጠረጴዛውም በታቦቱ ፊት ለፊት ይቀመጥ፤ ለእኔ የሚቀርበው የተቀደሰ ኅብስት ዘወትር በጠረጴዛው ላይ መኖር አለበት።


ገበታውና የመገልገያ ዕቃዎቹ በሙሉ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው የተቀደሰው ኅብስት፥


በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ ፊት ለፊት፥ ከእንጨት የተሠራ መሠዊያ የሚመስል ነገር ይታይ ነበር፤ እርሱም እኩልነት ያለው አራት ማእዘን ሲሆን፥ እያንዳንዱ ማእዘን ሁለት ክንድ ነበር፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ነበር፤ የማእዘን መደገፊያ ምሰሶዎቹ፥ መሠረቱና ጐኖቹ ሁሉ ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ ያም ሰው “ይህ በእግዚአብሔር ፊት የሚገኝ ጠረጴዛ ነው” አለኝ።


ነገር ግን ሁሉ ነገር በአግባብና በሥነ ሥርዓት ይሁን።


ሁለት ክፍሎች ያሉአት ድንኳን ተዘጋጅታ ነበር። መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት የነበረባት መጀመሪያይቱ ክፍል “ቅድስት” ትባል ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos