ዘፀአት 38:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰሜንም በኩል የአደባባዩ አሠራር እንደዚሁ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሜኑም ክፍል ቁመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር፤ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ የንሓስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰሜን በኩል መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቻቸው ሃያ የነሐስ እግሮቻቸውም ሃያ ነበሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰሜኑም ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ከናስም የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎችንና ሃያ እግሮችን፥ ለምሰሶዎችም የብር ኵላቦችንና ዘንጎችን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰሜኑም ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጆች፥ ከናስም የተሠራ ሀያ ምሰሶችንና ሀያ እግሮችን፥ ለምሰሶቹም የብር ኩላቦችንና ዘንጎችን አደረገ። |
በምዕራብ በኩል ኻያ ሁለት ሜትር ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ነበሩ፤ እነርሱም ዐሥር እግሮች ያሉአቸው ዐሥር ምሰሶዎች ነበሩአቸው፤ ምሰሶዎቹም ከብር የተሠሩ ኩላቦችና ዘንጎች ነበሩአቸው።