ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ሲሆን በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበደ ነበር።
ዘፀአት 30:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመሠዊያውን ጫፍ፥ አራት ጐኖቹንና ጒጦቹን ሁሉ በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ የወርቅ ክፈፍም አብጅለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላዩን፣ ጐኖቹን ሁሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለብጣቸው፤ ዙሪያውን የወርቅ ክፈፍ አብጅለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላዩን፥ የጎኖቹን ዙሪያ ሁሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ ዙሪያው የወርቅ አክሊል ታደርግለታለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወለሉንና የግድግዳውንም ዙሪያ፥ ቀንዶቹንም በጥሩ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የጥሩ ወርቅ ክፈፍ ታደርግለታለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላይኛውንና የግድግዳውንም ዙሪያ ቀንዶቹንም በጥሩ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ታደርግለታለህ። |
ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር፥ ሲሆን በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበደ ነበር።
ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰሎሞን የሚከተሉትን ዕቃዎች አሠራ፤ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ፥
ርዝመቱ አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር የጐኑ ስፋት አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር ከፍታውም ዘጠና ሳንቲ ሜትር ሆኖ የተስተካከለ አራት ማእዘን ይሁን። በአራቱም ማእዘን ያሉት ጒጦች ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ይሁኑ፤
የወርቅ ጥና የያዘ ሌላ መልአክ መጣና በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑ ፊት ባለው የወርቅ መሠዊያ ላይ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር የሚያቀርበው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።