ዘፀአት 26:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቀደሰው ድንኳን አንድ ይሆን ዘንድ ለእነዚህ ሁለት ክፍሎች ኀምሳ የወርቅ መያዣዎችን ሠርተህ በቀለበቶቹ አገጣጥማቸው።። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የመገናኛው ድንኳን አንድ ወጥ ይሆን ዘንድ መጋረጃዎቹን በአንድ ላይ ለማያያዝ ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሥራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምሳ የወርቅ መያዣዎችን ሥራ፤ ድንኳኑም አንድ ወጥ እንዲሆን መጋረጃዎቹን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምሳ የወርቅ መያዣዎች ሥራ፤ መጋረጃዎችን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው፤ ድንኳኑም አንድ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምሳ የወርቅ መያዣዎች ሥራ፤ ማደሪያውንም አንድ እንዲሆን መጋረጆችን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው። |
መጋረጃውንም በድንኳኑ ጣራ ላይ በተርታ በተደረደሩት መያዣዎች ሥር ታንጠለጥለዋለህ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች የያዘውንም የቃል ኪዳን ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ በኩል ታኖረዋለህ፤ በዚህ ዐይነት መጋረጃው ቅድስት የተባለውን ስፍራ ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል፤
በመጀመሪያው መጋረጃ መጀመሪያ ክፍል ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ በሁለተኛው መጋረጃ መጨረሻ ክፍል ላይ ከሌሎቹ ቀለበቶች ፊት ለፊት ኀምሳ ቀለበቶች አድርግ።
ከዚህ በኋላ የሚከተሉትን ዕቃዎች ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡአቸው፤ ድንኳኑንና የመገልገያ ዕቃዎቹን ሁሉ እነርሱም፦ ኩላቦቹ፥ ተራዳዎቹ መወርወሪያዎቹ፥ ምሰሶዎቹና የሚቆሙባቸው እግሮች፥
የተለያዩት የሰውነት ክፍሎች የሚገጣጠሙት በክርስቶስ ነው፤ አካልም በሙሉ የተያያዘው በመገጣጠሚያዎቹ ነው፤ ስለዚህ እያንዳንዱ የአካል ክፍል የተመደበለትን ተግባር በሚገባ ሲያከናውን አካል በሙሉ ያድጋል፤ በፍቅርም ይታነጻል።