ዘፀአት 26:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንኳኑ በስተ ጀርባ ባለው በምዕራብ በኩል፥ ስድስት ተራዳዎችን አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዳር በኩል ለሚገኘው ይኸውም በምዕራብ ጠርዝ ላለው የማደሪያው ድንኳን ስድስት ወጋግራዎች አብጅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለማደሪያውም በምዕራቡ ወገን በስተ ኋላ ስድስት ሳንቃዎችን አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለድንኳኑም በምዕራቡ በኩል በስተኋላ ስድስት ሳንቆች አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለማደሪያውም በምዕራቡ ወገን በስተ ኋላ ስድስት ሳንቆችን አድርግ። |