በአንድ በኩል ካለው መጋረጃ መጨረሻ ክፍል ጠርዝ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ በሌላም በኩል ካለው መጋረጃ መጨረሻ ጠርዝ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች አድርግ።
ዘፀአት 26:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀለበቶቹም ውስጥ ኀምሳ የነሐስ መያዣዎችን አስገባ፤ በዚህም ዐይነት ሁለቱን ክፍሎች በማገጣጠም አንድ ክዳን እንዲሆኑ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዐምሳ የንሓስ ማያያዣዎችን ሥራ፤ ድንኳኑን አንድ ወጥ አድርጎ ለማያያዝ በቀለበቶቹ ውስጥ ጨምራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምሳ የናስ መያዣዎችን ሥራ፥ መያዣዎቹንም ወደ ቀለበቶቹ አስገባቸው፥ ድንኳኑንም አጋጥመው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምሳም የናስ መያዣዎችን ሥራ፤ መያዣዎችንም ወደ ቀለበቶች አግባቸው፤ መጋረጃዎችንም አጋጥማቸው፤ አንድም ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምሳ የናስ መያዣዎችን ሥራ፥ መያዣዎችንም ወደ ቀለበቶች አግባቸው፥ ድንኳኑም አንድ እንዲሆን አጋጥመው። |
በአንድ በኩል ካለው መጋረጃ መጨረሻ ክፍል ጠርዝ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ በሌላም በኩል ካለው መጋረጃ መጨረሻ ጠርዝ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች አድርግ።