ዘፀአት 26:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንድ በኩል ካለው መጋረጃ መጨረሻ ክፍል ጠርዝ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ በሌላም በኩል ካለው መጋረጃ መጨረሻ ጠርዝ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንድ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ እንዲሁም በሌላ በኩል ባለው መጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አድርግ፤ በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አምሳ ቀለበቶች አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውጭ ከተጋጠሙት መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አምሳ ቀለበቶች አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አምሳ ቀለበቶች አድርግ። |
አምስቱን በአንድ በኩል፥ ስድስቱን በሌላ በኩል አድርገህ በአንድነት በማጋጠም ስፋቸው፤ ስድስተኛው መጋረጃ ታጥፎ ከፊት በኩል በድንኳኑ ላይ ይደረብ።
በመጀመሪያው ክፍል የመጀመሪያ መጋረጃ ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ እንዲሁም በሁለተኛው ክፍል መጨረሻ መጋረጃ ላይ ከሌሎቹ ቀለበቶች ፊት ለፊት የሚሆኑ ኀምሳ ቀለበቶች አደረጉ።