ባሕሩን በፊታቸው ለሁለት ከፈልክ፤ በደረቅ ምድርም ተሻገሩ፤ ድንጋይ ወደ ጥልቅ ባሕር እንደሚጣል፥ እነርሱን ያሳድዱ የነበሩትንም ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።
ዘፀአት 15:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥልቁ ባሕር አሰጠማቸው፤ እንደ ድንጋይም አቈልቊለው ወደ ባሕሩ ጥልቀት ወረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀላያትንም ለበሱ፤ እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ወረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀላያትም ከደኑአቸው፤ እንደ ድንጋይ ወደ ባሕር ጥልቀት ወረዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማዕበልም ከደናቸው፤ ወደ ባሕር ጥልቀት እንደ ድንጋይ ሰጠሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀላያትም ከደኑአቸው፤ ወደ ባሕር ጥልቀት እንደ ድንጋይ ሰጠሙ። |
ባሕሩን በፊታቸው ለሁለት ከፈልክ፤ በደረቅ ምድርም ተሻገሩ፤ ድንጋይ ወደ ጥልቅ ባሕር እንደሚጣል፥ እነርሱን ያሳድዱ የነበሩትንም ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።
ውሃውም ተመልሶ እስራኤላውያንን ይከተሉ የነበሩትን ሠረገሎችን፥ ፈረሰኞችንና መላውን የግብጽ ሠራዊት ሸፈነ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም።
አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በሥልጣንህ እንደ ድንጋይ ጸጥ አሉ።
“እግዚአብሔር ሆይ! ተጨንቄ ሳለሁ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም መለስክልኝ፤ ርዳታህን ለማግኘት ጥልቅ ከሆነው ከሙታን ዓለም ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ሰማኸኝ።
“ማንም ሰው በእኔ ከሚያምኑት ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያስት ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢጣልና ቢሰጥም ይሻለዋል።”
ከዚህ በኋላ አንድ ብርቱ መልአክ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚያኽል አንድ ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው፤ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ በኀይል ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህ ወዲህም ከቶ አትገኝም፤