ስለዚህ ሕዝቅያስ በዚህ መንገድ አያታላችሁ! ወደ ስሕተትም አይምራችሁ! ከቶ እርሱን አትመኑ! የማንም ሕዝብ አምላክ የራሱን ሕዝብ ከማንኛውም የአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ ሊያድን የቻለበት ጊዜ የለም፤ ይህም የእናንተ አምላክ እናንተን ሊያድን እንደማይችል የተረጋገጠ ነው።”
ዘፀአት 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “እስቲ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ የዐመፅ ሤራ ማቀዳችሁ ግልጥ ስለ ሆነ ሴቶቻችሁንና ልጆቻችሁን ይዛችሁ እንድትሄዱ አልፈቅድላችሁም! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም እንዲህ አለ፤ “ከሴቶቻችሁና ከልጆቻችሁ ጋራ እንድትሄዱ እለቅቃችኋለሁ፤ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሁን፤ ነገር ግን ተንኰል ዐስባችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ ከእናንተ ጋር ይሁን እናንተንና ልጆቻችሁን እለቅቃለሁ፥ ነገር ግን ክፉ ነገር በፊታችሁ እንደሚሆን ተመልከቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም አላቸው፥ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ እነሆ፥ እናንተን ስለቅ ልጆቻችሁንም መልቀቅ አለብኝን? ክፉ ነገር እንደሚገጥማችሁ ዕወቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም፦ “እናንተን ከልጆቻችሁ ጋር ስለቅቅ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ ነገር ግን ክፉ ነገር በአእምሮአችሁ እንዳለ እወቁ። |
ስለዚህ ሕዝቅያስ በዚህ መንገድ አያታላችሁ! ወደ ስሕተትም አይምራችሁ! ከቶ እርሱን አትመኑ! የማንም ሕዝብ አምላክ የራሱን ሕዝብ ከማንኛውም የአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ ሊያድን የቻለበት ጊዜ የለም፤ ይህም የእናንተ አምላክ እናንተን ሊያድን እንደማይችል የተረጋገጠ ነው።”
ንጉሡም ሙሴን ጠርቶ “ሄዳችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁም ከእናንተ ጋር መሄድ ይችላሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁና ፍየሎቻችሁ የቀንድ ከብቶቻችሁም እዚህ መቅረት ይኖርባቸዋል።”
ሙሴም “ሕፃን ልጆቻችንና ሽማግሌዎቻችን ሳይቀሩ ሁላችንም እንሄዳለን፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን፥ በጎቻችንንና ፍየሎቻችንን፥ የቀንድ ከብቶቻችንንም ሁሉ እንወስዳለን፤ በምንሄድበት ስፍራ ለእግዚአብሔር በዓል እናደርጋለን” ሲል መለሰ።