አዳምም፥ “እነሆ በመጨረሻ እርስዋ ከአጥንቶቼ የተገኘች አጥንት ናት፤ ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤ ከወንድ የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ።
ኤፌሶን 5:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገዛ ራሱን አካል የሚጠላ ማንም የለም፤ ይልቅስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን እንደሚያደርገው ዐይነት ራሱን ይመግባል፤ ይንከባከባልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ማንም የለም፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋል፤ ክርስቶስም ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው ልክ እንደዚሁ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም የራሱን እካል የሚጠላ ከቶ የለምና፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበውማል። ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው እንዲህ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቶ ሥጋውን መጥላት የሚቻለው የለም፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መገባት መግቡ፤ ጠብቁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። |
አዳምም፥ “እነሆ በመጨረሻ እርስዋ ከአጥንቶቼ የተገኘች አጥንት ናት፤ ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤ ከወንድ የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ።
እንደ እረኛ ለመንጋው እንክብካቤ ያደርጋል፤ ግልገሎቹን በአንድነት ይሰበስባል፤ በእጆቹም ዐቅፎ ይወስዳቸዋል፤ እናቶቻቸውንም በርኅራኄ ይመራቸዋል።
ዛፎች ያፈራሉ፤ እርሻዎች በቂ የእህል ምርት ይሰጣሉ፤ እያንዳንዱም በገዛ ራሱ ምድር በሰላም ይኖራል፤ የሕዝቤን ቀንበር ሰብሬ ባሪያ አድርገው ከሚገዙአቸው ጨቋኞች እጅ ነጻ ሳወጣቸው እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም ሆይ! አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ! ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ፥ እኔም የአንቺን ልጆች በአንድነት ልሰበስብ ስንት ጊዜ ፈቀድኩ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?