መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
ኤፌሶን 5:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ባልም የሚስቱ ራስ ነው፤ ደግሞም ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን አዳኝዋ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክርስቶስ፣ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደሆነ ባል የሚስት ራስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክርስቶስ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስዋ አዳኝዋም እንደ ሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። |
መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
“ምግብ ለሆድ፥ ሆድም ለምግብ ነው፤” ታዲያ፥ እግዚአብሔር ምግብንም፥ ሆድንም ያጠፋቸዋል፤ ነገር ግን ሰውነታችን ለጌታ ኢየሱስ፥ ጌታ ኢየሱስም ለሰውነታችን ስለ ሆነ ሰውነታችንን ለዝሙት ማዋል አይገባንም።
እንዲሁም እግዚአብሔር ከሞት ያስነሣውን፥ ከሚመጣው ቊጣ የሚያድነንን፥ የልጁን የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት እንዴት እንደምትጠባበቁም ይመሰክራሉ።
አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤