ከመከራ በቀር ያገኘሁባት ጥቅም ባለመኖሩ ሕይወት በእኔ ዘንድ ትርጒም አልተገኘላትም፤ ይህም ከንቱ ስለ ነበር ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ይቈጠራል።
መክብብ 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እኔ “በዚህ ሁኔታ ላይ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱት ይሻላሉ” አልኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም የቀድሞ ሙታን፣ ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ፣ ደስተኞች እንደ ሆኑ ተናገርሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም እስከ ዛሬ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን አመሰገንሁ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እስከ ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን አመሰገንኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እስከ ዛሬ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን አመሰገንሁ፥ |
ከመከራ በቀር ያገኘሁባት ጥቅም ባለመኖሩ ሕይወት በእኔ ዘንድ ትርጒም አልተገኘላትም፤ ይህም ከንቱ ስለ ነበር ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ይቈጠራል።
የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ስለ ንጉሥ ኢዮስያስ አታልቅሱ፤ በመሞቱም አትዘኑ፤ ነገር ግን የኢዮስያስ ልጅ ሻሉም፤ ዳግመኛ ወደማይመለስበት ቦታ ስለሚወሰድ፥ የትውልድ አገሩንም ዳግመኛ ስለማያይ፥ ለእርሱ ምርር ብላችሁ አልቅሱ።