ስለዚህ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት አዘዘ፤ ወዲያውኑ ከእስር ቤት ይዘውት መጡ፤ ጠጒሩን ተላጭቶ ልብሱን ከለወጠ በኋላ ወደ ንጉሡ ፊት ቀረበ።
መክብብ 4:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም እንኳ አንድ ሰው ከድኻ ቢወለድና እስረኛ የነበረ ቢሆንም ንጉሥ ለመሆን ይችላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወጣቱ ከእስር ቤት ወደ ንጉሥነት የመጣ ወይም በግዛቱ ውስጥ በድኽነት የተወለደ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም እንኳን ችግረኛ ሆኖ ቢወለድ፥ ከእስር ቤት ለመንገሥ ወጥቶአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንግሥቱ ችግረኛ ቢሆንም ከግዞት ቤት ለመንገሥ ወጥቶአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምንም በመንግሥቱ አገር ደግሞ ችግረኛ ሆኖ ቢወለድ፥ ከግዞቱ ቤት ወደ መንግሥት ወጥቶአልና። |
ስለዚህ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት አዘዘ፤ ወዲያውኑ ከእስር ቤት ይዘውት መጡ፤ ጠጒሩን ተላጭቶ ልብሱን ከለወጠ በኋላ ወደ ንጉሡ ፊት ቀረበ።
ንጉሥ ኢኮንያን ከእናቱ፥ ከልዑላን መሳፍንቱ፥ ከጦር አዛዦቹና ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች ጋር ቀርቦ ለባቢሎናውያን እጁን ሰጠ፤ ናቡከደነፆር በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ኢኮንያንን እስረኛ አድርጎ ያዘው፤
ይኸውም ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየ ልጆቹ በፊቱ ታረዱ፤ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ አሳወረው፤ እጆቹንም በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
ንግግሩን ገና ሳይጨርስ እንዲህ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ “ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ! የተላለፈብህን ውሳኔ ስማ! እነሆ፥ መንግሥትህ ከአንተ ተወስዳለች፤
እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።