መክብብ 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ልጆች እንዲደክሙበት እግዚአብሔር የሰጣቸውን የከባድ ሥራ ጭነት ተመለከትኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ይደክሙበት ዘንድ አምላክ የሰጣቸውን ከባድ የሥራ ጫና አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ይደክሙበት ዘንድ የሰጣቸውን ጥረት አይቻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ይደክሙበት ዘንድ የሰጣቸውን ድካም ሁሉ አይቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ይደክሙበት ዘንድ የሰጣቸውን ጥረት አይቻለሁ። |
የነፋስን አካሄድና የሰውም ሕይወት አፈጣጠር በእናቱ ማሕፀን እንዴት እንደሚጀመር እንደማታውቅ የሁሉ ነገር ፈጣሪ እግዚአብሔር ሥራውን እንዴት እንደሚያከናውን ማወቅ አትችልም።
እግዚአብሔር ደስ ለሚያሰኘው ሰው ብቻ ጥበብን፥ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል፤ ለኃጢአተኛ ሰው ግን ድካምን ብቻ ያተርፍለታል፤ ስለዚህም እርሱ ያከማቸውን ሀብት ሁሉ ምንም ላልደከመበት እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኝ ለሌላ ሰው ትቶለት እንዲያልፍ ያደርገዋል፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።
ወንድሞች ሆይ! እንዴት እንደ ሠራንና እንደ ደከምን ታውቃላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ በምናበሥርበት ጊዜ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን በመሥራት እንደክም ነበር።
የማንንም እንጀራ በብላሽ አልበላንም፤ ይልቅስ ከእናንተ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆንበት በማለት ሌሊትና ቀን በመድከምና በመልፋት እንሠራ ነበር።