ታዲያ እንዴት እንደገና የአንተን ትእዛዞች ጥሰን ከእነዚህ ዐመፀኞች ሕዝቦች ጋር ጋብቻ እንፈጽማለን? በዚህስ ምክንያት ምንም ቅሬታ ሳታስቀርልን እኛን በቊጣህ አታጠፋንምን?
ዘዳግም 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሲና በረሓ እንኳ እናንተን ለማጥፋት እስኪነሣሣ ድረስ እግዚአብሔርን በብርቱ አስቈጥታችሁታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኮሬብ እግዚአብሔርን ለቍጣ አነሣሣችሁት፤ እርሱም እናንተን ሊያጠፋችሁ እጅግ ተቈጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኮሬብም የጌታን ቁጣ ቀሰቀሳችሁ፥ ጌታም ሊያጠፋችሁ እስኪነሳ አስቆጣችሁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኮሬብ ደግሞ እግዚአብሔርን አሳዘናችሁት፤ እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ በእናንተ ላይ ተቈጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኮሬብ ደግሞ እግዚአብሔርን አስቆጣችሁ፤ እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ ተቆጣባችሁ። |
ታዲያ እንዴት እንደገና የአንተን ትእዛዞች ጥሰን ከእነዚህ ዐመፀኞች ሕዝቦች ጋር ጋብቻ እንፈጽማለን? በዚህስ ምክንያት ምንም ቅሬታ ሳታስቀርልን እኛን በቊጣህ አታጠፋንምን?
ነገር ግን እስራኤላውያን በበረሓ ሳሉ እንኳ በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚታዘዝለት ሁሉ ሕይወትን የሚያስገኝለትን ሕጌንና ሥርዓቴን ጣሱ፤ ፈጽመውም ሰንበትን አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ በመግለጥ ላጠፋቸው አስቤ ነበር፤