ዘዳግም 4:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስከ ሰማይ በሚደርስ የእሳት ነበልባልና ጥቅጥቅ ባለ የጢስ ደመና ወደተጋረደው ተራራ ግርጌ ቀርባችሁ ቆማችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራራው በጥቍር ደመናና በድቅድቅ ጨለማ ተውጦ ሳለ ነበልባሉ ሰማይ እስከሚደርስ ድረስ በተቃጠለ ጊዜ መጥታችሁ ከተራራው ግርጌ ቆማችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፥ እስከ ሰማይም ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፥ ጨለማም ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፤ ተራራውም እስከ ሰማይ ድረስ በእሳት ይነድድ ነበር፤ ጨለማና አውሎ ነፋስ፥ ድቅድቅ ጨለማም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፤ እስከ ሰማይም መካከል ድረስ አሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፤ ጨለማና ደመና ድቅድቅ ጨለማም ነበረ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን “እኔ ግዙፍ በሆነ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ስለዚህም ሕዝቡ እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር በመስማት ከአሁን ጀምሮ አንተ የምትለውን ሁሉ ያምናሉ።” ሙሴም ሕዝቡ የሰጠውን መልስ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤