ከኃጢአትዋ ብዛት የተነሣ እግዚአብሔር ችግር እንዲደርስባት አደረገ፤ ጠላቶችዋ ገዢዎችዋ ሆነዋል፤ ልጆችዋም በጠላት ተማርከው ተወስደዋል ጠላቶችዋ ግን ተሳክቶላቸዋል።
ዘዳግም 28:44 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጻተኞች ለአንተ ገንዘብ አበዳሪዎች ይሆናሉ፤ አንተ ግን ለእነርሱ የምታበድራቸው ገንዘብ አይኖርህም፤ በመጨረሻም እነርሱ እንደ ራስ መሪ ይሆናሉ፤ አንተ ግን እንደ ጅራት ወደ ኋላ ትቀራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ያበድርሃል እንጂ አንተ አታበድረውም። እርሱ ራስ ይሆናል፤ አንተ ግን ጅራት ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ያበድርሃል፤ አንተም ትበደረዋለህ። እርሱ ራስ ይሆናል፤ አንተ ግን ጅራት ትሆናለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ያበድርሃል፤ አንተ ግን አታበድረውም፤ እርሱ ራስ ይሆናል፤ አንተም ጅራት ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ያበድርሃል፥ አንተ ግን አታበድረውም፤ እርሱ ራስ ይሆናል፥ አንተም ጅራት ትሆናለህ። |
ከኃጢአትዋ ብዛት የተነሣ እግዚአብሔር ችግር እንዲደርስባት አደረገ፤ ጠላቶችዋ ገዢዎችዋ ሆነዋል፤ ልጆችዋም በጠላት ተማርከው ተወስደዋል ጠላቶችዋ ግን ተሳክቶላቸዋል።
እግዚአብሔር ያሰበውን ፈጸመ፤ ቀድሞ የተናገረውን ቃል ተግባራዊ አደረገ፤ ከረጅም ጊዜ በፊት በወሰነው መሠረት ያለ ርኅራኄ አፈራረሰ፤ ጠላት በእናንተ ላይ ደስ እንዲሰኝ አደረገ፤ የጠላቶቻችሁንም ኀይል አበረታ።