እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ እርስዋም ከእርሱ ተለይታ ሌላ ወንድ ካገባች በኋላ እንደገና መልሶ ሊያገባት ይችላልን? ይህ ቢደረግማ ፈጽሞ ምድርን የሚያረክስ ይሆናል። እስራኤል ሆይ! አንቺ ግን ብዙ ጣዖቶችን ወደሽ ነበር፤ አሁን ደግሞ እንደገና ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽ።
ዘዳግም 24:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለቱም መንገድ ቢሆን ያ የመጀመሪያ ባልዋ እንደገና ሊያገባት አይፈቀድለትም፤ እንደ ረከሰች አድርጎ ይቊጠራት፤ እርስዋን እንደገና ቢያገባ ይህ ድርጊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ስትኖሩ እንደዚህ ያለውን አስከፊ ኃጢአት መፈጸም አይገባችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፣ የረከሰች በመሆኗ እንደ ገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኀጢአት አታምጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ በኋላ የፈታት የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው። ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰደዳት የቀድሞ ባልዋ ከረከሰች በኋላ ደግሞ ያገባት ዘንድ አይገባውም፤ ያ በእግዚአብሔር የተጠላ ነውና፤ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር አታርክስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰደዳት የቀድሞ ባልዋ ከረከሰች በኋላ ደግሞ ያገባት ዘንድ አይገባውም፤ ያ በእግዚአብሔር የተጠላ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር አታርክስ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ እርስዋም ከእርሱ ተለይታ ሌላ ወንድ ካገባች በኋላ እንደገና መልሶ ሊያገባት ይችላልን? ይህ ቢደረግማ ፈጽሞ ምድርን የሚያረክስ ይሆናል። እስራኤል ሆይ! አንቺ ግን ብዙ ጣዖቶችን ወደሽ ነበር፤ አሁን ደግሞ እንደገና ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽ።
ሁለተኛውም ባል ስለሚጠላት የተፈታችበትን ምክንያት የሚገልጥ የፍች ደብዳቤ ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ያባርራታል፤ ወይም ሁለተኛው ባልዋ ይሞት ይሆናል፤
በእናንተም ምክንያት እኔን ተቈጣ፤ የዮርዳኖስንም ወንዝ ተሻግሬ እንዳልሄድና እርሱ የሚሰጣችሁን ያቺን ለምለም ምድር እንዳላይ በመሐላ አስታወቀኝ።