እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፥ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው።
ዘዳግም 22:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ባለቤቱ የሚኖርበት ቦታ ሩቅ ቢሆን፥ ወይም ባለቤቱ ማን እንደ ሆነ ካላወቅህ እንስሳውን ወደ ቤትህ ውሰደው፤ እርሱን ሊፈልግ በሚመጣበት ጊዜ ለባለቤቱ ስጠው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድምህ በአቅራቢያህ ባይኖር፣ ወይም የማን መሆኑን የማታውቅ ከሆነ፣ ባለቤቱ ፈልጎት እስኪመጣ ድረስ፣ ወደ ቤትህ ወስደህ ከአንተ ዘንድ አቈየው፤ ከዚያም መልሰህ ስጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘህ ወደ ቤትህ ትገባለህ፥ ወንድምህ እስኪፈልገው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣል፥ ለእርሱም ትመልሰዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘሃቸው ወደ ቤትህ ትገባለህ፤ ወንድምህ እስኪሻቸው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣሉ፤ ለእርሱም ትመልስለታለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘህ ወደ ቤትህ ትገባለህ፤ ወንድምህ እስኪሻው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣል፥ ለእርሱም ትመልሰዋለህ። |
እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፥ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው።
በዚህ ነገር ማንም ሰው አይተላለፍ፤ ሌላ አማኝን አይበድል፤ ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን ጌታ ይቀጣቸዋል።