ዘዳግም 22:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልጅትዋ ወላጆች ልጅቱ ድንግል መሆንዋን የሚያረጋግጥላትን ማስረጃ አምጥተው በከተማይቱ ሸንጎ ለሚገኙት መሪዎች ያሳዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጅቱ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዪቱ በር ወዳሉት አለቆች ይምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የብላቴናይቱ አባትና እናት የድንግልናዋን ምልክት ወስደው በበሩ በአደባባይ ወደ ተቀመጡ ወደ ከተማ ሽማግሌዎች ያምጡት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብላቴናዪቱ አባትና እናት የልጃቸውን የድንግልናዋን ልብስ ወስደው በበሩ አደባባይ ወደ ተቀመጡ ወደ ከተማ ሽማግሌዎች ያምጡት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብላቴናይቱ አባትና እናት የድንግልናዋን ምልክት ወስደው በበሩ በአደባባይ ወደ ተቀመጡ ወደ ከተማ ሽማግሌዎች ያምጡት፤ |