ዘዳግም 22:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ይህችን ሴት አግብቼ ክብረ ንጽሕናዋን አላገኘሁም’ ብሎ በሐሰት ክስ ስምዋን ቢያጠፋ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሟንም በማጥፋት፣ “ይህችን ሴት አገባኋት፤ ዳሩ ግን በደረስሁባት ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁም” ቢል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነውር ነገር አውርቶ፦ ‘እኔ ይህችን ሴት ሚስት አድርጌ አገባኋት፥ በደርስሁባትም ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁባትም’ ብሎ በክፉ ስም ቢያሳጣት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነውር ነገርም ቢያመጣባት፥ እኔ ይህችን ሴት ሚስቴ አድርጌ አገባኋት፤ በደረስሁባትም ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁባትም ብሎ ክፉ ስም ቢያወጣባት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የነውር ነገር አውርቶ፦ እኔ ይህችን ሴት ሚስት አድርጌ አገባኋት፥ በደርስሁባትም ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁባትም ብሎ በክፉ ስም ቢያሳጣት፥ |
በተጨማሪም አንድ መቶ ጥሬ ብር መቀጫ አስከፍለው ገንዘቡን ለልጅትዋ አባት ይስጡት፤ ያ ሰው ድንግል የሆነችውን የአንዲት እስራኤላዊት ልጃገረድ ስም አጒድፎአል፤ ከዚህም በቀር የእርሱ ሚስት ሆና ትኖራለች፤ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ሊፈታት አይገባም።
ስለዚህ በዕድሜአቸው ያልገፉ መበለቶች እንዲያገቡ፥ ልጆችን እንዲወልዱ፥ ቤታቸውንም በሚገባ እንዲያስተዳድሩ እመክራለሁ፤ በዚህ ዐይነት ጠላት ለስም ማጥፋት ምክንያት ያጣል።