ዘዳግም 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚህ ከመድረሳችሁም በፊት እግዚአብሔር በዚያ በረሓ ምን እንዳደረገ ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምድረ በዳው አንሥቶ እዚህ እስከምትደርሱ ድረስ፣ ለእናንተ ያደረገላችሁን ያዩት ልጆቻችሁ አልነበሩም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድረ በዳው አንሥቶ እዚህ እስከምትደርሱ ድረስ፥ ለእናንተ ያደረገላችሁን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደዚህ ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደዚህ ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን፥ |
እናንተን ባሳደዱአችሁ ጊዜ የግብጽን ሠራዊት ከነፈረሶቻቸውና ከነሠረገሎቻቸው በቀይ ባሕር በማስጠም እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ለዘለቄታው እንደ ደመሰሳቸው አይታችኋል።
ከሮቤል ነገድ ወገን የኤልያብ ልጆች በሆኑት በዳታንና በአቤሮን ላይ ያደረገውን አስታውሱ፤ እስራኤላውያን ሁሉ በዐይናቸው እያዩ መሬት ተከፍታ እነርሱንና ቤተሰቦቻቸውን፥ ድንኳኖቻቸውንና ሕይወት ያለውና የእነርሱ የነበረውን ሁሉ ዋጠቻቸው።