ዘዳግም 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም ‘ያቀረብከው ሐሳብ መልካም ነው’ ብላችሁ መልስ ሰጥታችሁኝ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም፣ “ይደረግ ዘንድ ያቀረብኸው ሐሳብ መልካም ነው” ብላችሁ መለሳችሁልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም፦ ‘እናደርገው ዘንድ የተናገርኸው ይህ ነገር መልካም ነው፥’ ብላችሁ መለሳችሁልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም፦ ‘እናደርገው ዘንድ የተናገርኸው ይህ ነገር መልካም ነው’ ብላችሁ መልሳችሁ ነገራችሁኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም፦ እናደርገው ዘንድ የተናገርኸው ይህ ነገር መልካም ነው ብላችሁ መለሳችሁልኝ። |
ስለዚህም ከእያንዳንዱ ነገድ የመረጣችኋቸውን የሥራ ልምድ ያላቸውን ዐዋቂዎች መሪዎች ተቀብዬ ሾምኩላችሁ። ከእነርሱም አንዳንዶቹ የሺህ አለቆች፥ አንዳንዶቹ የመቶ አለቆች፥ አንዳንዶቹም የኀምሳና የዐሥር አለቆች ሆነው የተሾሙ ነበሩ። ለነገዶችም ሁሉ ሌሎችንም ሹማምንት ሾምኩ።