ዘዳግም 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእያንዳንዱ ነገድ የማስተዋል ጥበብ ያላቸውንና የሥራ ልምድ ያላቸውን ሰዎች ምረጡ፤ እኔም በእናንተ ላይ እሾማቸዋለሁ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበበኞችን፣ አስተዋዮችንና የተከበሩ ሰዎችን ከየነገዳችሁ ምረጡ፤ እኔም በእናንተ ላይ እሾማቸዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ ከየነገዳችሁ ጥበበኞች፥ አስተዋዮች፥ አዋቂዎች የሆኑትን ሰዎች ምረጡ፥ እኔም በላያችሁ አለቆች አደርጋቸዋለሁ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ ከየነገዳችሁ ጥበበኞች፥ አስተዋዮችም፥ ዐዋቂዎችም የሆኑትን ሰዎች አምጡ፤ እኔም በላያችሁ አለቆች አደርጋቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ ከየነገዳችሁ ጥበበኞች አስተዋዮችም አዋቂዎችም የሆኑትን ሰዎች ምረጡ፥ እኔም በላያችሁ አለቆች አደርጋቸዋለሁ። |
በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው።