“ቀንዱ የሚናገረውን የዕብሪታዊ ንግግር ድምፅ ሰምቼ ተመለከትኩ፤ እየተመለከትኩም ሳለ አውሬው ተይዞ ከተገደለ በኋላ ወደ እሳት በመጣል አካሉ እንዲጠፋ ተደረገ።
ዳንኤል 7:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም በዚህ አውሬ ራስ ላይ ስለ ነበሩት ዐሥር ቀንዶችና በኋላ ስለ በቀለው ትንሽ ቀንድ፥ እንዲሁም ለትንሹ ቀንድ ቦታ ለመተው ተነቃቅለው ስለ ወደቁት ሦስት ቀንዶች ለማወቅ ፈለግኹ። ይህ ትንሽ ቀንድ ዐይኖችና አፍ ነበረው፤ ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ አስፈሪ ሆኖ በትዕቢት ይናገር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም በራሱ ላይ ስላሉት ዐሥር ቀንዶች፣ ከመካከላቸው ብቅ ስላለው ቀንድና ከዚሁ ቀንድ ፊት ስለ ተነቃቀሉት ሦስት ቀንዶች፣ እንደዚሁም ከሌሎች ስለ በለጠው የሰው ዐይኖች የሚመስሉ ዐይኖች፣ በትዕቢትም የሚናገር አፍ ስለ ነበሩት ስለዚሁ ቀንድ ማወቅ ፈለግሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራስዋም ላይ ስለ ነበሩ ስለ አሥር ቀንዶች፥ በኋላም ስለ ወጣው፥ በፊቱም ሦስቱ ስለ ወደቁ፥ ዓይኖችና ትዕቢት የተናገረ አፍ ስለ ነበሩት፥ መልኩም ከሌሎች ስለ በለጠ ስለ ሌላው ቀንድ እውነቱን ለማወቅ ፈቀድሁ። |
“ቀንዱ የሚናገረውን የዕብሪታዊ ንግግር ድምፅ ሰምቼ ተመለከትኩ፤ እየተመለከትኩም ሳለ አውሬው ተይዞ ከተገደለ በኋላ ወደ እሳት በመጣል አካሉ እንዲጠፋ ተደረገ።
“ከዚህ በኋላ ከሌሎቹ አውሬዎች ሁሉ ልዩ ስለ ነበረው ስለ አራተኛው አውሬ በይበልጥ ለማወቅ ፈለግኹ፤ ይህ አውሬ እጅግ አስፈሪ የሆነ፥ ዐድኖ ያገኘውን ሁሉ በብረት ጥርሶቹና በነሐስ ጥፍሮቹ ሰባብሮና ቦጫጭቆ የሚበላ፥ የተረፈውንም በእግሩ የሚረጋግጥ ነበር።
“እርሱም ትርጒሙን እንዲህ ሲል አስረዳኝ፤ ‘አራተኛው አውሬ በምድር ላይ የሚነሣ አራተኛ መንግሥት ነው፤ ይህ መንግሥት ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ በመሆኑ ምድርን ሁሉ በመውረር ረግጦና ቀጥቅጦ ይገዛል።
“ከዚያ በኋላ አራተኛውን አውሬ አየሁ፤ እርሱም አስፈሪ፥ አስደንጋጭና በጣም ኀይለኛ ነበር፤ ይህም አውሬ የሚቦጫጭቅባቸውና የሚሰባብርባቸው ታላላቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት። የተረፈውንም በእግሮቹ ይረግጠው ነበር፤ ካለፉትም አውሬዎች ሁሉ የተለየ ሆኖ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።
እኔም ስለ ቀንዶቹ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ ከቀንዶቹ መካከል ሌላ አንድ ትንሽ ቀንድ ወጣ፤ ለእርሱም ቦታ ለመልቀቅ ከፊተኞቹ ቀንዶች ሦስቱ ተነቀሉ፤ ይህም ትንሽ ቀንድ የሰው ዐይኖችና በትዕቢት የሚናገር አንደበት ነበረው።
እንዲሁም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ፤ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች የነበሩት ትልቅ ቀይ ዘንዶ ታየ፤ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ደፍቶ ነበር፤