እንግዲህ እግዚአብሔር በሰው እጅ ጣቶች ልኮ እነዚህን ቃላት እንዲጽፉ ያደረገው ስለዚህ ነው።
ስለዚህ እርሱ ጽሕፈቱን የጻፈውን እጅ ላከ።
ስለዚህም እነዚህ የእጅ ጣቶች ከእርሱ ዘንድ ተልከዋል፥ ይህም ጽሕፈት ተጽፎአል።
“የጽሑፉም ንባብ ‘ማኔ! ማኔ! ቴቄል! ኡፋርሲን’ የሚል ነው።
የሰው እጅ ጣቶች በድንገት ታይተው በቤተ መቅደሱ መቅረዝ ፊት ለፊት ባለው በተለሰነው የቤተ መንግሥቱ ግድግዳ ላይ መጻፍ ጀመሩ፤ እነዚያም ጣቶች በሚጽፉበት ጊዜ ንጉሡ አየ።