እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዓለምን ስለ ክፋቱ፥ ክፉዎችን ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የኲራተኞችን ማን አለብኝነት አዋርዳለሁ፤ የትዕቢተኛውንም ጭካኔ አጠፋለሁ።
ዳንኤል 2:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ንጉሥ ሆይ! እጅግ የሚያንጸባርቅና ብልጭልጭታው ለማየት የሚያስፈራ ታላቅ ምስል በፊትህ ቆሞ አየህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ንጉሥ ሆይ፤ በፊት ለፊትህ ግዙፍ የሆነ፣ የሚያብረቀርቅና የሚያስፈራ ታላቅ ምስል ቆሞ አየህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ ታላቅ ምስል አየህ፥ ይህም ምስል ታላቅና ብልጭልጭታው የበዛ ነበረ፥ በፊትህም ቆሞ ነበር፥ መልኩም ግሩም ነበረ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዓለምን ስለ ክፋቱ፥ ክፉዎችን ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የኲራተኞችን ማን አለብኝነት አዋርዳለሁ፤ የትዕቢተኛውንም ጭካኔ አጠፋለሁ።
በአንተ ላይ አደጋ የሚጥሉ ጨካኞች ጠላቶችን አመጣብሃለሁ፤ እነርሱ በጥበብህና በብልኀትህ ያገኘኸውንና ያከማቸኸውን ያማረ ነገር ሁሉ ያጠፋሉ።
“አእምሮዬ እንደ ተመለሰልኝ ወዲያውኑ የመንግሥቴ ክብርና ግርማ ማዕርጉም ሁሉ እንደገና ተሰጠኝ፤ አማካሪዎቼና መኳንንቴ በደስታ ተቀበሉኝ፤ ከቀድሞው የበለጠ ክብር ተጨምሮልኝ በንጉሥነቴ ጸናሁ።