በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ አጥቶ ስለ ነበር በቤተ መንግሥቱ መዝገብ ላይ የሰፈሩትን የታሪክ ማስታወሻዎች አምጥተው ያነቡለት ዘንድ ትእዛዝ ሰጠ።
ዳንኤል 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አየ፤ በጣምም ስለ ተጨነቀ እንቅልፍ አጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም ዐለመ፤ መንፈሱ ታወከ፤ እንቅልፍም ከርሱ ራቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናቡከደነፆርም በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ናቡከደነፆር ሕልም አለመ፥ መንፈሱም ታወከ፥ እንቅልፉም ከእርሱ ራቀ። |
በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ አጥቶ ስለ ነበር በቤተ መንግሥቱ መዝገብ ላይ የሰፈሩትን የታሪክ ማስታወሻዎች አምጥተው ያነቡለት ዘንድ ትእዛዝ ሰጠ።
የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ተናገረኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ነበር፤
የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ፤ ዳንኤል ሕልምና ራእይ አየ፤ ከዚያም በኋላ ያየውን ሕልም ጻፈ።