“የሶርያም ንጉሥ ወደ አገሩ ተመልሶ ከበፊቱ የበለጠ የጦር ሠራዊት ያደራጃል፤ ከጥቂት ዓመቶችም በኋላ ሠራዊቱን ከተሟላ ትጥቅ ጋር አሰልፎ ይመጣል።
ዳንኤል 11:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ብዙ ሰዎች በግብጽ ንጉሥ ላይ ያምፃሉ፤ ዳንኤል ሆይ! በዚህ ራእይ የታየው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ከአንተም ወገኖች አንዳንድ የዐመፅ ሰዎች ሁከት ያስነሣሉ፤ ነገር ግን አይሳካላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያም ዘመን ብዙዎች በደቡብ ንጉሥ ላይ ይነሣሉ፤ ራእዩ ይፈጸም ዘንድ፣ ከሕዝብህ መካከል ዐመፀኛ የሆኑ ሰዎች ይነሣሉ፤ ነገር ግን አይሳካላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዘመን ብዙ ሰዎች በደቡብ ንጉሥ ላይ ይነሣሉ፥ ከሕዝብህም መካከል የዓመፅ ልጆች ራእዩን ያጸኑ ዘንድ ይነሣሉ፥ ነገር ግን ይወድቃሉ። |
“የሶርያም ንጉሥ ወደ አገሩ ተመልሶ ከበፊቱ የበለጠ የጦር ሠራዊት ያደራጃል፤ ከጥቂት ዓመቶችም በኋላ ሠራዊቱን ከተሟላ ትጥቅ ጋር አሰልፎ ይመጣል።
ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ በአንዲት በተመሸገች ከተማ ላይ ከበባ አድርጎ ይይዛታል፤ የግብጽም ወታደሮች እርሱን መቋቋም ይሳናቸዋል፤ ከእነርሱ ምርጥ የሆኑት እንኳ እርሱን ለመቋቋም በቂ ኀይል አይኖራቸውም።
ዕቅዱን እንዲፈጽሙ ይህን ሐሳብ በልባቸው ያኖረ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም እነርሱ በአንድ ሐሳብ ይስማማሉ፤ የመንገሥ ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ያስረክባሉ።