‘በተለይም አገልጋይህ ያዕቆብ ከበስተኋላ እየመጣ ነው’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። ይህንንም ያለበት ምክንያት “እኔ ከመድረሴ በፊት በሚደርስለት ስጦታ ቊጣውን አበርድ ይሆናል፤ በኋላም በማገኘው ጊዜ በደስታ ይቀበለኛል” በሚል ሐሳብ ነው።
ዳንኤል 10:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ አገልጋይህ ስሆን ከአንተ ከጌታዬ ጋር መነጋገር እንዴት እችላለሁ? መተንፈስ እስከሚያቅተኝ ድረስ እጅግ ደክሜአለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታዬ ሆይ፤ ጕልበቴ ከዳኝ፤ መተንፈስም አቅቶኛል፤ እኔ አገልጋይህ ከአንተ ጋራ መነጋገር እንዴት እችላለሁ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ የጌታዬ ባሪያ ከዚህ ከጌታዬ ጋር ይናገር ዘንድ እንዴት ይችላል? አሁንም ኃይል አጣሁ፥ እስትንፋስም አልቀረልኝም አልሁት። |
‘በተለይም አገልጋይህ ያዕቆብ ከበስተኋላ እየመጣ ነው’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። ይህንንም ያለበት ምክንያት “እኔ ከመድረሴ በፊት በሚደርስለት ስጦታ ቊጣውን አበርድ ይሆናል፤ በኋላም በማገኘው ጊዜ በደስታ ይቀበለኛል” በሚል ሐሳብ ነው።
በዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል እጅግ ከመደንገጡና በሐሳብ ከመታወኩ የተነሣ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለ፤ ንጉሡም “ብልጣሶር ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ አያስጨንቅህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ ለአንተ መሆኑ ቀርቶ ለጠላቶችህ ቢሆን በወደድሁ ነበር።
ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ፥ ‘እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ)፥ ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤’ ብሎታል።
ጌዴዎን ያየው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በተገነዘበ ጊዜ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! የአንተን መልአክ ፊት ለፊት አይቼአለሁ ወዮልኝ!” አለ።