የጲርሁስ ልጅ ሶጳጥሮስ ከቤርያ፥ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ ከተሰሎንቄ፥ ጋይዮስ ከደርቤ፥ ጢሞቴዎስ፥ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ከእስያ አብረውት ሄዱ።
ቈላስይስ 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቲኪቆስ ስለ እኔ ጉዳይ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል፤ እርሱ ተወዳጅ ወንድም፥ ታማኝ አገልጋይና በጌታ ሥራም የአገልግሎት ጓደኛዬ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቲኪቆስ ስላለሁበት ሁኔታ በሙሉ ይነግራችኋል፤ እርሱ የተወደደ ወንድምና ታማኝ አገልጋይ፣ በጌታም ዐብሮኝ ባሪያ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተወደደ ወንድምና የታመነ አገልጋይ በጌታም አብሮኝ ባርያ የሆነ ቲኪቆስ እኔ ስላለሁበት ሁኔታ ሁሉ ይነግራችኋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተወደደ ወንድማችንና የታመነ አገልጋይ፥ በጌታ ሥራም ተባባሪያችን የሆነ ቲኪቆስ የእኔን ዜና ይነግራችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተወደደ ወንድምና የታመነ አገልጋይ በጌታም አብሮኝ ባሪያ የሆነ ቲኪቆስ ኑሮዬን ሁሉ ያስታውቃችኋል፤ |
የጲርሁስ ልጅ ሶጳጥሮስ ከቤርያ፥ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ ከተሰሎንቄ፥ ጋይዮስ ከደርቤ፥ ጢሞቴዎስ፥ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ከእስያ አብረውት ሄዱ።
እንዲሁም እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜን ኤጳፍሮዲቱስን ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ እርሱ ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ጓደኛዬ ሆኖ ሲሠራ የቈየ ነው።
የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በመንፈሳዊ ሕይወት በማደግ ጸንታችሁ እንድትቆሙና የእግዚአብሔርንም ፈቃድ በሙሉ እንድትፈጽሙ እርሱ ስለ እናንተ በጸሎቱ ዘወትር ይጸልያል።
ከእርሱም ጋር የእናንተ ወገን የሆነው የታመነውና የተወደደው ወንድም ኦኔሲሞስ ወደ እናንተ ይመጣል፤ እነርሱ በዚህ ስፍራ ስላለው ነገር ሁሉ ያስታውቋችኋል።
አርጤማስን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ በምልክበት ጊዜ አንተ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ ለመምጣት ፍጠን፤ እኔ ክረምቱን እዚያ ለማሳለፍ ወስኜአለሁ።