ቈላስይስ 4:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በመንፈሳዊ ሕይወት በማደግ ጸንታችሁ እንድትቆሙና የእግዚአብሔርንም ፈቃድ በሙሉ እንድትፈጽሙ እርሱ ስለ እናንተ በጸሎቱ ዘወትር ይጸልያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ ወገን የሆነው የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ እርሱም ፍጹም ጠንክራችሁና ሙሉ በሙሉ ተረጋግታችሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ዘወትር ስለ እናንተ በጸሎት እየተጋደለ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ ወገን የሚሆን ኤጳፍራስም ሰላም ይላችኋል፥ እርሱ የክርስቶስ አገልጋይ ነው፤ እግዚአብሔር በሚወደው ነገር ሁሉ ምሉኣንና ፍጹማን እንድትሆኑ፥ ስለ እናንተ ዘወትር ይጸልያል፤ ይማልዳልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል። |
ወንድሞቼ ሆይ! ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ በትግሌ እንድትረዱኝ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እለምናችኋለሁ።
ነገር ግን በመንፈሳዊ ሕይወት ለበሰሉት በጥበብ ቃል እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የምንናገረው የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም መጨረሻቸው ጥፋት የሚሆነውን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም።
በተረፈውስ ወንድሞቼ ሆይ! ደኅና ሁኑ! አኗኗራችሁን አስተካክሉ፤ ምክሬን ተከተሉ፤ እርስ በእርሳችሁ ተስማሙ፤ በሰላምም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
ታዲያ፥ እኔ የምፈልገው ሰው እንዲያመሰግነኝ ነውን? ወይስ እግዚአብሔር እንዲያመሰግነኝ? ወይስ ሰውን ደስ ለማሰኘት የምፈልግ መስሎአችሁ ይሆን? ሰዎችን ለማስደሰት የምፈልግ ብሆን ኖሮ የክርስቶስ አገልጋይ ባልሆንኩም ነበር።
አሁን ግን ቅዱሳንና ንጹሓን፥ ነቀፋም የሌለባችሁ አድርጎ በፊቱ ሊያቀርባችሁ፥ ልጁ በሥጋ በመሞቱ ምክንያት እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቃችሁ።
እያንዳንዱ ሰው በክርስቶስ ብቁ ሰው እንዲሆን አድርገን ለማቅረብ ለሰው ሁሉ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምከር ስለ ክርስቶስ እንሰብካለን።
ስለዚህ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምሮ እናንተ በመንፈሳዊ ጥበብና ማስተዋል ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምትገነዘቡበት ሙሉ ዕውቀት እንዲኖራችሁ ለእናንተ ከመጸለይና እግዚአብሔርን ከመለመን አላቋረጥንም።
ከእርሱም ጋር የእናንተ ወገን የሆነው የታመነውና የተወደደው ወንድም ኦኔሲሞስ ወደ እናንተ ይመጣል፤ እነርሱ በዚህ ስፍራ ስላለው ነገር ሁሉ ያስታውቋችኋል።
ራሱ የሰላም አምላክ በሁሉ ነገር ይቀድሳችሁ፤ መንፈሳችሁ፥ ነፍሳችሁ፥ አካላችሁ በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚመጣበት ቀን ያለ ነቀፋ ተጠብቆ ይኑር።
ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።
በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሆነው ከያዕቆብ የተላከ መልእክት፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤